በስቶክሆልም ከተማ ዉስጥ ለሚኖሩ አረጋዉያን እንክብካቤ

በስቶክአሆልም ከተማ ዉስጥ የአረጋዉያን እንክብካቤ፡ 65 ዓመት ለሞልዎት እና በዕለት ተዕለት ኑሮዎ ዉስጥ ድጋፍ እና እርዳታ ለሚፈልጉ ወይም ወይም ሌላ መኖርያ ቤት ለሚፈልጉት ነዉ።

ለአረጋዉያን እንክብካቤ ማመልከቻ ያቅርቡ

በአረጋዉያን እንክብካቤ ዉስጥ ለአብዛኛዎቹ ኣስተዋፅኦ ለማግኘት እራስዎን ማመልከት አለብዎት። በእርስዎ ፍላጎት መሰረት
ባማድረረግ ድጋፍን የሚወስነዉ፡ የዲስትሪክቱ አስተዳደር የእርዳታ ቢሮ ጸሃፊ ነዉ።

እርስዎ በሚኖርበት አዉራጃ ዉስጥ ካለዉ የበጎ አድራጎት መኮንን ጋር ለመገናኘት፡ አረጋዉያን በቀጥታ (ኤልድረ ዲረክት)
ይዱዎታል።

ስልክ ቁጥር፡ 08-80 65 65
ኢ-ሜል፡ aldredirekt@stockholm.se

የእርዳታ ዉሳኔዎን አንዴ ከተቀበሉ፣ የትኛዉን ፈጻሚ መቅጠር እንደሚፈልጉ መምረጥ ይችላሉ። ሁለቱም፡ ማለት የማዘጋፈጃ ቤት
እና የግል ኮንትራክተሮች አሉ

የደህንነት ማንቂያ (አላርም)

በደህንነት ማንቂያ ደወል፡ በመናንናዉም ጊዜ በቀን ለእርዳታ ማንቃት (መደወል) ይችላሉ። የማንቂያ ሰዓቱን ሲጫኑ፡
ከስቶክሆልም ከታማ ማንቂያ መቀበያ ጋር ይገናኛሉ።

የቤት አገልግሎት

የቤት አገልግሎቱ በቀን ዉስጥ ብዙ ጊዜ ከማጽዳት እና በወር ለተወሰኑ ሰአታት ምግብ ከማብሰል ጀምሮ እስከ አጠቃላይ
እንክብካቤ ድረስ ባሉት ነገሮች ሁሉ ሊረድዎ ይችላል። በቤትዎ እንዲቆዩ እና በዕለት ተዕለት ሕይዎትዎ ዉስጥ ደህንነት
እንዲሰማዎት፡ የቤት አግልግሎት ሊረዳዎ ይችላል።

ቁልፍ አልባ የቤት አገልግሎት

ቁልፍ አልባ የቤት ዉስጥ እንክብካቤ፡ ደህንነት ይጨምራል እና የቤት ዉስጥ እንክብካቤ ላላችሁ አገልግሎቱን ያሻሽላል። የቤት
አገልግሎት ቁልፎች፡ በዲጂታል ቁልፍ ተተክተዋል እና እርስዎ የቤት አገልግሎት ያላችሁ መደበኛ ቁልፍዎን መጠቀማችሁን
ትቀጥላላችሁ።

የቀን እንቅስቃሴዎች

በማህበራዊ ግንኙነት ወይም በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ ለመሳተፍ፡ ወደ አንድ የቀን እንቅስቃሴ መምጣት ይችላሉ።
ካስፈለገዎት ደግሞ ከ እና ወደ የእለት እንቅስቃሴዎች ጉዞ እንዲሁ ተካትቷል።

የእንክብካቤ እና የማስታመም መኖርያ ቤቶች

በእንክብካቤ እና የማስታመም መኖርያ ቤት ዉስጥ የሃያ ኣራት ሰዓት አገልግሎት እንክብካቤ አልዎት። ማረፊያዉ የሚፈልጉትን
እርዳታ ሁሉ ያካትታል።

Uppdaterad